Advert for the selection of story writers

ማስታወቂያ

ቀን ፡-  ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም.

መዝጊያ ቀን፡-  ሐምሌ 20  ቀን 2014 ዓ.ም.

ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር-ኢትዮጵያ ለትርፍ ያልተቋቋመና መንግስታዊ ያልሆነ አለም አቀፍ የግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን፣እትዮጵያ ውስጥ ከ1992 —/ም ጀምሮ በአገራችን ዋና ዋና የጤናና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ አስተማሪና አዝናኝ የሚዲያ እና የአትመት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር-ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅትም በሴቶች ላይ በሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት እና ጎጂ ድርጊቶች ዙሪያ ፕሮጀክት ነድፎ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎችን በማከናውን ላይ ይገኛል። ከነዚህም ተግባራት አንዱ በአውነተኛ ታሪኮች ላይ ተመርኩዘው የሚጻፉ የአጫጭር ድርሰቶችን ስብስብ የያዝ መጽሃፍ ማዘጋጀትና ማሳተም በመሆኑ መ/ቤታችን ችሎታ ያላቸውን ደራሲያን አወዳድሮ ታሪኮችን ለማጻፍና መጽሃፉን አዘጋጅቶ ለማሳተም እቅድ ይዟል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ባለሙያዎች ማምልክቻችሁን፤ እስከዛሬ ስለሰራችኋቸውን ስራዎች ማረጋገጫ በማቅረብ እስክ ሃምሌ 20 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር-ኢትዮጵያ ቢሮ ከዚሁ በታች በተመለከተው አድራሻ በካል በመምጣት ወይም በኢሜል እድራሻ እንድታመለክቱ እንገልጻለን።

ደራሲያን የሚያሟሏቸው መስፈርቶች

  1. ከዚህ ቀደም የሥነጽሑፍ ሥራ ያሳተሙ ፣
  2. ለአንድ ሳምንት በተመረጡ ክልሎችና ወረዳዎች በመስክ በመቆየት ጉዳቱ ወይም ችግሩ የደረሰባቸውን ባለታሪኮች ቃለመጠይቅ በማድረግ መረጃ ለመሰብሰብ ፈቃደኛ የሆኑ፣
  3. በአጭር ልቦለድ ቅርጽ እውነተኛ ታሪክ አጻጻፍ በፖፕሌሽን ሚዲያ በተመረጡ የሥነጽሑፍ ባለሙያዎች የሚሰጣቸውን መመሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚችሉ፣
  4. ስለተመረጡት ርዕሰ ጉዳዮች በባለሙያዎች የሚሰጡ ገለጻዎች ላይ ለመገኘት የሚችሉ፣
  5. የባለታሪኮቹን ምስጢር የሚጠብቁ፣ የግል ሰብዕናቸውን የሚያከብሩ የፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተርን የአሠራር ሥነምግባር የሚጠብቁ፣
  6. ድርሰቶቻቸውን በተያዘ የጊዜ ገደብ ለማስረከብ የሚስማሙ፣
  7. ለውድድር እሚቀርቡ ድርሰቶች ከዚህ በፊት በየትኛውም መገናኛ ብዙኃን ያልቀረቡ ወጥ ሥራዎች መሆን አለባቸው፡፡

አድራሻ

ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው በተቋሙ ዋና /ቤት መካነ ኢየሱስ ህንፃ 7 ፎቅ በአካል በመገኘት ቢሮ ቁጥር B706  ወይም ኢሜል rahelbernardo@populationmedia.org

ስልክ ቁጥር 0115520990

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *