Yechereta Mastawekia
ማስታወቂያ
ቀን ፡- ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም.
መዝጊያ ቀን፡- ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም.
ፖፑሌሽን ሚድያ ሴንተር፟ (PMC)፣ ዋና ተቋሙን በአሜሪካ ሀገር መሠረት አድርጎ የተመሰረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ አለማቀፋዊ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነዉ።
ፖፑሌሽን ሚድያ ሴንተር፟ ኢትዮጵያ (PMC-E ) ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ጋር በመተባበር ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት መካከል ስርዓተ-ፆታን መሰረት ያደረገ የውኃ፣ የአካባቢ እና የግልና ንጽህና አጠባበቅ እንዲሁም የስርዓተ-ምግብ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ በጥናት ላይ የተመሰረተ የመልቲሚዲያ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በተመረጡ ክልሎችና ወረዳዎች ላይ ይተገብራል።
ድርጅቱ በዩኒሴፍ ድጋፍ እያካሃደ ላለዉ የውኃ፣ የአካባቢ እና የግልና ንጽህና አጠባበቅ/ WASH/ እና የስርዓተ -ምግብ ዋና ባህሪያት ላይ ለት/ቤት ግድግዳ ስዕል ቅብ ስራ ብቁ ከሆኑ ግለሰቦች/ንዑስ ተቋራጮች በቀረበ ሥራ ዋጋ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የሥራው ርዕስ፡ ሥርዓተ ፆታን መሠረት ያደረገ የውኃ፣ የአካባቢ እና የግልና ንጽህና አጠባበቅ /WASH/ እና የስርዓተ ምግብ-ፕሮጀክት ለትምህርት ቤት የግድግዳ ላይ ስዕል ዝግጅትና ቅብ ሥራ ነው፡፡
የንዑስ ኮንትራት ሥራው ውል ስምምነቱ እንደተፈረመ ወዲያውኑ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
በመሆኑም ለሥራው የሚያስፈልገውን ዝርዝር ቴክኒካልና እና የፋይናንሺያል ፕሮፖዛሎችን በማዘጋጀት በታሸገ ኤንቨሎፕ አዲስ አበባ ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው በተቋሙ ዋና መ/ቤት መካነ ኢየሱስ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት ወይም ኢሜል rahelbernardo@populationmedia.org “የትምህርት ቤት የግድግዳ ላይ የሥዕል ቅብ ለመወዳደር” ብሎ ማቅረብ ይቻላል።
You can get the full details from the file below.