Advocacy Workshop on “FGM and Child marriage” to Community Scholars
ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር በደቡብ ክልል ከሚያከናውናቸው የሚዲያ ተግባራት በተጨማሪ የአቅም ማጎልበት ሥልጠናዎችንም ያካሂዳል። ለሁለት ቀናት የሚቆይ እና ትኩረቱን በሴት ልጅ ብልት ትልተላ እና በታዳጊነት የሚፈጸም ጋብቻን ጎጂነት የበለጠ ለማስገንዘብ ለቀበሌ ሥራ አስኪያጆች እና በተለያየ ሃላፊነት ላይ ላሉ አካላት የምክክር እና የግንዛቤ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል። ሥልጠናው ከስልጤ ዞን ከዳሎቻ እና ጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ ለተውጣጡ 40 ለሚሆኑ ቀበሌዎች ተወካዮች በቡታጅራ ካፍ ሆቴል እየተሰጠ ሲሆን ዛሬ ግንቦት 10, 2014 ይጠናቀቃል።